Police Program 11-02-2011 E.C Part-3

More Video

የተከበራችሁ የሃገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ፖሊሶችና አጋር የፀጥታ አካላት፣ የተከበራችሁ መላው የፌዴራል ፖሊስ አመራርና አባላት በአሁኑ ወቅት ሃገራችን ኢትዮጵያ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ዘላቂነት ያለው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ፋታ በማይሰጥ ወቅታዊ የመሠረተ-ልማት ግንባታ ስራዎች ጎዳና በመራመድ ላይ ትገኛለች፡፡ እነዚህ ሃገራዊ እርምጃዎች ቀንደኛ ጠላታችን የሆነውን ድህነትና ኋላቀርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሸነፍ የሚያስችሉ የማይላሉና ሁሌም በመጠንም ሆነ በጥራት እያደጉ መሄድ ያለባቸውና የሚገባቸው ትጥቆች መሆናቸው ሁላችንም በሚገባ የምንገነዘበው ሃገራዊ ግብና አቅጣጫ መሆኑ እሙን ነው፡፡ እነዚህ ሃገራዊ የልማትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደቶቻችን በተያዘላቸው አቅጣጫ፣ፍጥነትና ጥራት እንዲጓዙ ለማስቻል ደግሞ አስተማማኝ ሠላምና ደህንነት የማረጋገጡ ጉዳይ ወሳኝና ግንባር ቀደም ተግባር መሆኑ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህን የሃገራችንን አስተማማኝ ሠላምና ደህንነት የመጠበቅና የማረጋገጥ ጉዳይ በአጠቃላይ የመላው

Pages: 1  2  3