መረጃ ስለኛ

የኢትዬጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የኢትዬጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስትንና ሕገ-መንግስቱን መሠረት አድርገው የሚወጡ ሕጐችን አክብሮ የሚያስከብር የፖሊስ ተቋም በተቻለ መልክ ማደራጀት በማስፈለጉ፣ ሀገሪቱ የተያያዘችውን የሰላም የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ለማፋጠን በሚደረገው ሀገራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የበኩሉን ድርሻ ሊያበረክት የሚችል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ የፖሊስ ተቋም በተሻለ ሁኔታ መገንባት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ገለልተኛ የሆነና ሕብረተሰቡን በእኩልነት የሚያገለግል በፖሊሳዊ ሰነ-ምግባሩ የታነፀ ብቃትና ጥራት ያለው አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል የፖሊስ ተቋም በአዲስ መልክ ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑ፣ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መልካም አስተዳደርና ስነ-ምግባርን ለማስፈን ይቻል ዘንድ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዋጅ ቁጥር 313/1995 ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ በኢትዬጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55/1 መሰረት የሚከተለው ታውጃል፡፡ ክፍል አንድ ጠቅላላ 1.አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ የኢትዬጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዋጅ ቁጥር --------/2ዐዐ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ 2.ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡- 1. ?#4840;ፖሊስ አባል?#4635;ለት መሰረታዊ የሆነ የፖሊስ ሙያ ስልጠና ተሰጥቶት በኢትዬጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የፌዴራል ፖሊስ አባል ነው፡፡ 2.?#4634;ኒስትር?ወይም ?#4634;ኒስቴር?ማለት እንደ ቅደም ተከተሉ የፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስትር ወይም ሚኒስቴር ነው፡፡ 3.?#4936;ቃድ?ማለት ስለጦር መሳሪያ ምዝገባና አያያዝ፣በግል ጥበቃ አገልግሎት ለተሰማሩ ድርጅቶች፣ለልማት ስራ አገልግሎት የሚውሉ ፈንጂዎች፣የፎረንሲክ ምርመራ ስራዎች ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሚሰጥ ፈቃድ ነው፡፡ 4.?#4768;ውራ ጐዳና?ማለት የኢትዬጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሚያስተዳድራቸው እና አውራ ጐዳና ብሎ የሚሰይመው መንገድ ነው፡፡ 3. ስያሜ የኢትዬጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን /ኢ.ፌ.ፖ.ኮ/ ተብሎ ይጠራል፡፡ ስለኢትዬጵያ ፌዴራል ፖሊስ መቋቋም 1. ዋና መስሪያ ቤት 1. የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ይሆናል፡፡ 2.ኮሚሽኑ እንደ አስፈላጊነቱ በክልሎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማቋቋም ይችላል፡፡ 2. ዓላማ የሀገሪቱን ሕገ-መንግስትና ሌሎች ህጐችን በማክበርና በማስከበር ሕብረተሰቡን በወንጀል መከላከልና ምርመራ በማሳተፍ የመንግስትና የሕዝብን ሠላምና ደህንነት መጠበቅና ማረጋገጥ ነው፡፡ 3. ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል 1. በሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱ፣በመንግስትና በሀገር ፀጥታ፣በሰብዓዊ መብት ላይ የሚፈፀሙ ማናቸውም ዓይነት የወንጀል ስጋቶችና ድርጊቶችን ይከላከላል ይመረምራል፣ 2.የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ/1/ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ከክልል አቅም በላይ የሆነ የፀጥታ ወይም በሚመለከታቸው ክልሎች ሕግና ስርዓትን ያስከብራል፣ 3.በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የስልጣን ክልል ስር የሚወድቁ ወንጀሎችን ይከላከላል ይመረምራል፣ 4.ለከፍተኛ የፌዴራሉ መንግስት ባለስልጣናት እና ለውጭ አገር እንግዶችና ዲኘሎማቶች ጥበቃ ያደርጋል፣ 5.በፌዴራል መንግስት ጥቅሞችና ተቋሞች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ይከላከላል ይመረምራል፣ 6.የጠረፍ እና የድንበር ኬላዎች ደህንነትን፣የደረቅ ወደቦች፣የአየር ማረፊያዎችን፣የነዳጅ ማጠራቀሚያዎችን/ዴፖ/የባቡር መስመሮችን፣ከፍተኛ ድልድዬችንና የመገናኛ አውታሮችን፣ከፍተኛ የኃይል ማመንጫዎችን የማዕድን ማውጫ ቦታዎችን እና ሌሎች የፌዴራል መንግስት ተቋሞችን ይጠብቃል፣ 7. የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ይቆጣጠራል፣ተጠርጣሪዎችን አድኖ በመያዝ ለህግ ያቀርባል፣የኮንትሮባንድ እቃዎችን በመያዝ ለባለስልጣኑ ያስረክባል፣ተላላፊ የጉምሩክ እቃዎችንና ተሽከርካሪዎችን ያጅባል፣የጉሙሩክ መጋዘኖችን ይጠብቃል፣የታክስ ባለእዳዎችን ንብረት የመያዝና የመሸጥ ስርዓት በሕግ መሰረት ሲከናወን ፀጥታና ስነ-ስርዓት ያስከብራል፣ 8. በውጪ ሀገር መንግስት ተቋማትና ዜጐች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ይከላከላል ይመረምራል፣ 9. የሀገሪቱን ጥቅሞች በሚነኩ ጉዳዬች ላይ በውጪ ሀገር የሚፈፀሙ ማናቸውንም ወንጀሎች ይመረምራል፣ 10. ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሲከሰቱ እና ድንገተኛ የፀጥታ አለመረጋጋት ሲፈጠር የተጐዱ ሰዎችን በመርዳት፣ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን እና ሕግን በማስከበር ሌሎች ጉዳዬች ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና የፀጥታ አላላትን በማስተባበር በበላይነት ይመራል፣ 11. በተጓዥ ቼክ፣በባንክ ገንዘቦችና ሃብቶች ላይ የሃሰት ገንዘብና ሰነዶችን በመስራት የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ይከላከላል የመረምራል፣ 12. ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ ከኮምፒዩተር ስርዓት ጋር የተያያዙ የኢንተርኔት የስልክና የሳይበር ወንጀሎችን ይመረምራል፣ 13. በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰላማዊ ሰዎችንና በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን የአሻራ ሪከርዶችን በማዕከል ይይዛል፣ከወንጀል ነፃ ማስረጃ ይሰጣል፣ 14. በፎረንሲክ ሳይንስ ማስረጃዎች ላይ ምርመራ ያደርጋል፣ስለመረመረው ጉዳይ ማስረጃ ይሰጣል፣ለፍርድ ቤት ወይም ለጠያቂው አካል ቀርቦ የሙያ ምስክርነት ይሰጣል፣ 15. በፎረንሲክ ሳይንስ ምርመራ ነክ ጉዳዬች ከክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡ 16. በአስረጂነት አገልግሎት ሊሰጡ የማይችሉ የወንጀል ምርመራ መዛግብቶችን፣ሰነዶችን፣አሻራዎችን እና ተያያዥነት ያላቸው ሪከርዶች ከብሄራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃህፍት ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት እንዲወገዱ ያደርጋል ዝርዝር አፈፃፀሙ መመሪያ ይወሰናል፣ 17. በግለሰብ ወይም በተደራጀ መልክ የሚፈፀም ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና እገታ፣የአደገኛ ዕፆች ዝውውርና ስርጭትን፣የአይሮኘላንና የመርከብ ጠለፋ፣ዘረፋ፣ውንብድና፣አሸባሪነት እና የፀጥቃ ማደፍረስ ወንጀሎችን ይከላከላል ይመረምራል፣ 18. የሽብርተኝነት ድርጊት ሊፈፀም እንደሚችል በቂ እና ምክንያታዊ ጥርጣሬ ሲኖርና ድርጊቱንም ቀድሞ ለመከላከል ድንገተኛ ፍተሻ ማድረግ አስፈላጊነቱ ሲታመንበት በማንኛውም ጊዜ በተጠረጠረው አካባቢ ያለን ተሽከርካሪ እና እግረኛን በማስቆም ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ተጠርጣሪ ሰዎችና መረጃዎችን መያዝና ምርመራ ማድረግ ይችላል፣ 19. የሀገርን ብሄራዊ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ወንጀሎችን ለመከላከል እና ለመመርመር የሚረዳ መሆኑ በሚገባ የታመነበትን ማስረጃ ወይም መረጃ ከማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት፣መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት፣የገንዘብና ልዩ ልዩ የልማት ተቋማት፣የግል ድርጅት ወይም ግለሰብ በመጠየቅ ወንጀሎችን ይመረምራል፡፡ ማስረጃ ወይም መረጃ የተጠየቀውም አካል ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መረጃውን ወይም ማስረጃውን የመስጠት ግዴታ አለበት፣ 20. ኮሚሽኑ ተልዕኮውን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ የወንጀል መከላከልና ምርመራ ስራዎችን ለመስራትና ለማጐልበት እንዲሁም የፖሊስ ሙያ ብቃትና አገልግሎት ለማሻሻል የሚረዱ ጥናቶችን ያጠናል፣ያስጠናል በስራ ላይም እንዲውሉ ያደርጋል፣ 21. ወንጀልን ለመከላከልና ለመመርመር የሚረዱ ሀገር አቀፍ የፖሊሲ፣የስትራቴጂና የስታንዳርዳይዜሽን ነክ ጉዳዬችን ያስጠናል፣የጥናቱን ውጤትም ለፌዴራልና ለክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባኤ ያቀርባል፣ 22. በፖሊስ ምልመላ እና ቀጠራ፣በትምህርትና ስልጠና፣በማዕረግ ዕድገት አሰጣጥ፣በጡረታ ዕድሜ እና በሌሎች ጉዳዬች ሀገር አቀፍ እስታንዳርዶችን ያወጣል፣ 23. በሀገር አቀፍ ደረጃ ስለወንጀልና መንስኤዎቻቸው፣ስለ ትራፊክ አደጋ መረጃዎችን እና ስታትስቲክሶችን ያሰባስባል፣ይተነትናል የመፍትሄ ሀሳቦችን ያቀርባል መረጃውን ለሚመለከተው አካል ይሰጣል፣ 24. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ትኩረት በመስጠት ለክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች የትምህርት፣የሙያ ስልጠና፣የቴክኒክ እና የምክር ድጋፍ ይሰጣል፣ 25. ኮሚሽኑ ለአባላቱ በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር ተከታታይነት ያለው ትምህርትና ስልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፣ 26. ኮሚሽኑ ለሃገር ውስጥ፣ለውጭ ሀገር ሰዎችና ተቋማት ስልጠና ይሰጣል፣ 27. የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችንና የስፖርት ማበልፀጊያ ማዕከላትን ያደራጃል 28. በፍርድ ቤት የሚሰጠውን ትዕዛዝ ወይም ውሳኔይፈፅማል፣ 29. የወንጀል ምርመራን በተመለከተ ከፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ጋር በቅንጅት ይሰራል፣ 30. ኮሚሽኑ፡- ሀ. የጦር መሳሪያ ይመዘግባል፣በግለሰቦችና በድርጅቶች ሊያዙ የሚገባቸውንና የማይገባቸውን የጦር መሳሪያዎችን ይለያል፣ፈቃድ ይሰጣል፣ ለ. የጥበቃ ስራ ለሚያከናውኑ የግል ተቋማት ፈቃድ ይሰጣል ስራቸውንም በአግባቡ ማከናወናቸውን ይከታተላል፣ ሐ. ለልማት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ፈንጂዎችን ፈቃድ ይሰጣል፣ያጅባል፣ጥበቃ እና ቁጥጥር ያደርጋል፣ መ. የፎረንሲክ ሳይንስ ምርመራ ስራዎችን ለመስራት ልዩ ዕውቀትና የሙያ ብቃት ማስረጃ ላላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ስለ ፖሊስ አመራመር ስነ-ምግባር ስልጠና በመስጠት በቅንጅት መስራት የሚያስችል የስራ ፈቃድ ይሰጣል፣ 31. ከፀጥታ አካላት ጋር የመረጃ ልውውጥ በማድረግ በቅንጅት ይሰራል፣በጥናትና ስልጠና ይደጋገፋል፣ 32. ለኮሚሽኑ አባላት የሚያገለግል የደመወዝ እስኬል እና ልዩ ልዩ አበሎችን አጥንቶ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፣ 33. ለአባላቱ እንደየስራ ባህሪያቸው አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ቢሮዎችንና የመኖሪያ ካምፖች ይሰራል፣ 34. በከተማ ውስጥ የሚሰሩ ልዩ ልዩ የግንባታ ኘላኖች ከወንጀልና ከድንገተኛ አደጋዎች ለመከላከል አመችነታቸውን ያረጋግጣል፣ 35. ሀገሪቱ የሚቀርብላትን ዓለማቀፍ የሰላም ማስከበር ጥሪ በአግባቡ ለመወጣት የሚችል የሰላም አስከባሪ ፖሊስ ያዘጋጃል፣ 36. ባለሞተር ተሽከርካሪ መንዳት የሚያስችል ስልጠና እና የመንጃ ፈቃድ ለፖሊስ አባላት ይሰጣል፣የመንጃ ፈቃዱም በትራንስፖርት ባለስልጣን እውቅና እንዲሰጠው ያደርጋል፣ 37. በአውራ ጐዳናዎች ላይ የመንገድ ላይ የትራፊክ ደንቦችና መመሪያዎች መከበራቸውን ይቆጣጠራል፣የትራፊክ አደጋዎችን የመረምራል፣ 38. በፌዴራልና በክልሎች የማሰልጠኛ ማዕከላት ያቋቁማል፣ 39. የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች በሚሰጣቸው ውክልና መሰረት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቁ የወንጀል ጉዳዬችን ሲመረምሩና ሲከላከሉ ተጠሪነታቸው ለኮሚሽኑ ይሆናል፣ 40. ኮሚሽኑ የመሳሪያ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥን በተመለከተ ለክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች እንደአስፈላጊነቱ የስልጣን ውክልና ሊሰጥ ይችላል፣ተጠሪነታቸውም ለኮሚሽኑ ይሆናል፡፡ 41. ፖሊስ ነክ በሆኑ ጉዳዬች ላይ አግባብ ካላቸው የውጪ ሀገር መንግስታት ፖሊስ ተቋማት መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል፣ 42. ከዓለም አቀፍ ፖሊስ ጋር ግንኙነት በመፍጠር የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፣በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ የሆኑ ወንጀለኞችን መረጃ ለክልሎች ፖሊስ ኮሚሽኖች ያሰራጫል፣ተከታትሎ ይይዛል፣ 43. ውል ይዋዋላል፣የንብረት ባለቤት ይሆናል፣በራሱ ስም ይከሳል፣ይከሰሳል፡፡ 4. የኮሚሽኑ አቋም ኮሚሽኑ፡- 1. በመንግስት የሚሾሙ አንድ ኮሚሽነር ጄኔራል እና ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራሎች 2. የኮሚሽኑ ማኔጅመንት አባላት እና 3. አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች የፖሊስና የሲቪል አባላት ይኖሩበታል፡፡ የሰው ሃብት ልማትና አስተዳደር 5. ምልመላ 1. ለኮሚሽኑ አባልነት ለመመልመል ፈቃደኛ የሆነ ማንኛውም ኢትዬጵያዊ የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት ይኖርበታል፣ ሀ. ለኢትዬጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት ታማኝ የሆነ፣ ለ. የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ፣ ሐ. በፖሊስነት ለመመልመል የሚያበቃ የትምህርት ደረጃ፣አካላዊ ብቃትና የተሟላ ጤንነት ያለው፣ መ. መልካም ስነ-ምግባር ያለው፣ ሰ. የወንጀል የጥፋተኛነት ሪኮርድ የሌለው፣ ረ. ዕድሜው ከ18 ዓመት ያላነሰ፣ 6. ስልጠና 1. በኮሚሽኑ አባልነት የሚቀጠር ማንኛውም ሰው ስራውን ከመጀመሩ በፊት መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና ይሰጠዋል፣ 2. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ/1/ የተደነገገው ቢኖርም በልዩ ሙያ ለሚቀጠሩ ሰራተኞች የስራ ባሕሪያቸውን ከግምት ያስገባ ስልጠና ይሰጣል፣ 3. ኮሚሽኑ ለአባላቱ ተከታታይነት ያለው ትምህርት እና በስራ ላይ ስልጠና ይሰጣል፡፡ 7. ቅጥር በኮሚሽኑ የሚሰጠውን ስልጠና አጠናቆ ቃለመሐላ በመፈፀም የተመረቀ ሰልጣኝ ከተመለመለበቅ ቀን ጀምሮ የኮሚሽኑ አባል ይሆናል፡፡ 8. ቃለመሀላ ስለመፈፀም በፖሊስነት የተቀጠረ ማንኛውም አባል ለኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት ታማኝ በመሆን የተጣለበትን ሕዝባዊ አደራና ሙያዊ ሀላፊነት ለመወጣት ቃለ መሐላ ይፈፅማል፡፡ የቃለመሀላው ይዘት በደንብ ይወሰናል፡፡ 9. የአገልግሎት ዘመን 1. ማንኛውም የኮሚሽኑ አባል የግዴታ አገልግሎት ዘመን 7 ዓመት ይሆናል፡፡ዝርዝር አፈፃፀሙ በደንብ ይወሰናል፡፡ 2. ማንኛውም የኮሚሽኑ አባል ቅጥር በሚከተሉት ምክንያቶች ይቋረጣል፣ ሀ. በደንቡ መሰረት የስንብት ጥያቄ ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ፣ ለ. በህመም ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት ለስራው ብቁ አለመሆኑ በሕክምና ቦርድ ሲረጋገጥ፣ ሐ. በስራ አፈፃፀም ወይም በዲሲኘሊን ጥፋት፣ መ. በፍርድ ቤት በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ በደንቡ መሰረት ወንጀሉ ለስራው ብቁ አያደርገውም ተብሎ ሲወሰን፣ዝርዝሩ በደንብ ይወሰናል፣ ሠ. በሀሰት የትምህርት ወይም የስራ ልምድ ማስረጃ ተጠቅሞ ሲገኝ፣ ረ. በዕድሜ ምክንያት በጡረታ ሲገለል፣ ሰ. በሞት ሲለይ፡፡ 10. መብት 1. ማንኛውም የኮሚሽኑ አባል፡- ሀ. በመንግስት በሚፀድቅ የደመወዝ ስኬል መሰረት ደመወዝ ያገኛል፣ ለ. በኮሚሽኑ የመተዳደሪያ ደንብ መሰረት ቀለብ፣ልዩ ልዩ አበሎች፣የደንብ ልብስና የሕክምና አገልግሎት ያገኛል፣ ሐ. ቢያንስ 25 ዓመት ያገለገለ የኮሚሽኑ አባል በራሱ ፈቃድ አገልግሎት ለማቋረጥ ጥያቄ ካቀረበና የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሊደርስ 5 ዓመት ከሚቀረው ጊዜ ጀምሮ እስከ እድሜ ልኩ የአገልግሎት ጡረታ አበል ይከፈለዋል፣ መ. የጡረታ መብት ይኖረዋል፣ ሠ. ከፖሊሳዊ ተግባሩ ጋር በተገናኘ ሁኔታ ስራውን በማከናወን ላይ እያለ ለሚደርስበት የወንጀልም ሆነ የፍታብሄር ተጠያቂነት በመስሪያ ቤቱ የሕግ ባለሙያዎች የጥብቅና አገልግሎት ያገኛል፣ዝርዝር አፈፃፀሙ በደንብ ይወሰናል፣ ረ. ከስራው ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሚደርስበት ዘላቂ ጉዳት ወይም በከፊል የመስራት ችሎታውን የጣ አባል የጡረታ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ እንደ ጉዳቱ መጠን የጉዳት ካሳ ይከፈለዋል፣ 11. ግዴታ ማንኛውም የኮሚሽኑ አባል፡- 1. ሕገ-መንግስቱን እና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ከማንኛውም አደጋ መደበቅ አለበት፣ 2. በሕገ-መንግስቱ የተረጋገጡትን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሳይሸራረፉ ማክበር እና ማስከበር አለበት፣ 3. የመንግስት ፖሊሲዎችን መፈፀምና ማስፈፀም አለበት፣ 4. የወንጀል ሕግና የሕጉ ማስፈፀሚያ የሆነው የስነ-ስርዓት ሕግ መሰረት በማድረግ ስራውን ማከናወን አለበት፣ 5. የሀገሪቷንና በስራው አጋጣሚ ያወቃቸውን የተቋሙን ምስጢሮች መጠበቅ አለበት፣ 6. መላው እውቀቱን፣ችሎታውንና አቅሙን ለተቋሙ ዓላማ ማዋል አለበት፣ 7. ከፖሊስ ተግባርና ኃላፊነት ጋር በተያያዘ ከበላይ አመራር የሚሰጡትን ህጋዊ ትዕዛዞች መፈፀም አለበት፣ 8. የህዝብና የመንግስት ንብረቶችን በአግባቡ የመጠበቅ እና ለስራ የተሰጡትን ንብረቶች ለታለመለት ስራ ብቻ ማዋል አለበት፣ 9. የሚጠበቅበትን ተግባር በትጋትና በታማኝነት መፈፀም አለበት፣ 10. ከሙስናና ከብልሹ አሰራር ራሱን ማራቅ አለበት፣ 11. ፖሊሳዊ ስራዉን ሲያከናውን ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡ 12. ሰባት ዓመት አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ 1ዐ. የማዕረግ ደርጃዎች በኮሚሽኑ ውስጥ የሚኖሩ የማዕረግ ደረጃዎች፡- 1. ኮንስታብል 2. ረዳት ሳጅን 3. ምክትል ሳጅን 4. ሳጅን 5. ዋና ሳጅን 6. ረዳት ኢንስፔክተር 7. ምክትል ኢንስፔክተር 8. ኢንስፔክተር 9. ዋና ኢንስፔክተር 10. ምክትል ኮማንደር 11. ኮማንደር 12. ረዳት ኮሚሽነር 13. ምክትል ኮሚሽነር 14. ኮሚሽነር 15. ምክትል ኮሚሽነር ዴኔራል 16. ኮሚሽነር ጄኔራል 11. ስለኮሚሽኑ አቤቱታ ሰሚ በኮሚሽኑ ውስጥ የሕዝብና የአባላት አቤቱታ ሰሚ አካል ይቋቋማል፣ዝርዝሩም በደንብና በመመሪያ ይወሰናል፡፡ 12. በኮሚሽኑና በክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች መካከል ስለሚኖረው የስራ ግንኙነት 1. ኮሚሽኑና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች በየበኩላቸው የሚኖራቸው ነፃነት እንደተጠበቀ ሆኖ በመካከላቸው የሚኖረውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ ጉባኤ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል፡፡ 2. የኮሚሽኑና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች በኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጄኔራል ሰብሳቢነት የሚመራ የጋራ ጉባኤ ይኖራቸዋል፡፡ 3. የጉባኤው ስልጣንና ተግባር፡- ሀ. የወንጀል ስጋትንና የወንጀል ድርጊትን ለመቀነስ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ያወጣል፣ይወስናል፣አፈፃፀሙንም ይገመግማል፣ ለ. የወንጀል ምርመራ ስራ ሂደት ማስረጃ መር እንዲሆንና የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ መብት በማክበር የሚከናወንበትን ዘዴ ይቀይሳል ተግባራዊ ስለመሆኑ ተገቢውን ቁጥጥርና ክትትል ያደርጋል፣ ሐ. በፖሊስ ምልመላ እና ቀጠራ፣በትምህርትና ስልጠና፣በማዕረግ ዕድገት አሰ ጣጥ በደመወዝና ልዩ ልዩ አበሎች አከፋፈል፣በትጥቅ፣በደንብ ልብስ አለባበስ በስንብት፣በጡረታ ዕድሜ እና በመሳሰሉት ጉዳዬች ወጥነት/እስታንድ/እንዲኖር በጋራ ይወስናል አፈፃፀሙንም ይከታተላል ይቆጣጠራል፣ መ. ዘመናዊ የመረጃ ስርዓት በመዘርጋት ስለፀጥታ ስጋት፣ስለተፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች፣ስለፎረንሲክ ምርመራ ውጤቶች፣የትራፊክ አደጋዎች ሪፖርት እና እስታትስቲካዊ መረጃዎችን በተከታታይነት ይለዋወጣል፣ ሠ. ኮሚሽኑ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ትኩረት በመስጠት ድጋፍ ያደርጋል፣ ረ. የወንጀል መከላከልና የምርመራ ስራዎችን በቅንጅትና በመደጋገፍ ይሰራል፣ ሰ. የፖሊስ አባላትን ተቋማዊ አመለካከትና አንድነት ለማጠናከር የስፖርትና ሌሎች ውድድሮች እንደካሄዱ ያደርጋል፣ ሸ. በዓመት ሁለት ጊዜ የጋራ ስብሰባ ያደርጋል፣ ቀ. የጉባኤው አባላት የግልና የጋራ ተጠያቂነት አለባቸው፣ በ. ስለ አሠራሩና አመራሩ የውስጥ መመሪያ ያወጣል፣ 13. ስለአዲስ አበባና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች 1. የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች በዋነኛነት ለኮሚሽኑ እና በውክልና ለየከተሞቻቸው አስተዳደር ተጠሪ ይሆናሉ፣ 2. የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች በጀት በየከተሞቻቸው አስተዳደር ምክር ቤቶች ይመደባል፣ 3. የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች ዓመታዊ ዕቅዳቸውንና የስራ አፈፃፀማቸውን ለኮሚሽኑና ለየከተሞቻቸው አስተዳደር ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡ 14. አሠራር 1. በኮሚሽኑ መዋቅር በየደረጃው ባሉት ኃላፊዎችና ሠራተኞች የቡድን አሠራር ዋና የተግባር አፈፆፀም አቅጣጫ ይሆናል፡፡ የቡድን አሠራሮች የጋራና የግል ኃላፊነትን ያስከትላሉ፣ 2. በኮሚሽኑ መዋቅር በየደረጃው የሚገኙ ኃላፊዎች በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት በመወሰን ኃለፊነታቸውን የመወጣት ግዴታ አለባቸው 3. የኮሚሽኑ አሰራር የተጠያቂነትና የግልጽነት መርህን የተከተለ መሆን ይኖርበታል፣ 4. የኮሚሽኑ አሠራር የሕዝብ ተሳትፎን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት፣ 5. የኮሚሽኑ አሰራር የገለልተኝነት የአሠራር መርህ የተከተለ ይሆናል፡፡ 15. የፖሊስ ስልጣን በውክልና ስለመስጠት 1. ልዩ ሙያ ለሚጠይቁ ጉዳዬች በፌዴራል የመንግስት ሠራተኞች አዋጅና አግባብ ባላቸው ሌሎች አዋጆች ለሚተዳደሩ የመንግስት ድርጅቶችና ሠራተኞች የፖሊስ ስልጣን በውክልና ሊሰጥ ይችላል፣ 2. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ /1/ ድንጋጌ መሰረት የሚሰጠው የፖሊስ ስልጣን ለጉዳዩ አስፈላጊ በሆነው መጠን ብቻ ይሆናል፡፡ 16. የተከለከሉ ድርጊቶች 1. ማናቸውም ኢሰብአዊ ወይም ክብርን የሚነካ አያያዝና ድርጊት፣ 2. በዘር፣በብሔር፣በብሔረሰብ፣በቀለም፣በፆታ፣በቋንቋ፣በሀይማኖት፣በፖለቲካ፣በማህበራዊ አመጣጥ፣በሀብት፣በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ 17. የተሻሩና ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ሕጐች 1. የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዋጅ ቁጥር 313/1995 በዚህ አዋጅ ተሽሯል፣ 2. ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሕግ በዚህ አዋጅ ላይ በተጠቀሱት ጉዳዬች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ 18. ደንብ የማውጣት ስልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈፀም ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡

የኮሚሽነሩ መልእክት
የድምፅ ዜና

የምስል ዜና
Download