ከባንክ እንደተደወለ አስመስለው የተለያዩ ስልኮችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ ሚስጥር ቁጥር በመቀበል በማጭበርበር ከግለሰቦች አካውንት ብር ከሚመዘብሩ ወንጀለኞች ህብረተሰቡ እንዲጠበቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ኅዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም(ኢፌፖሚ) ከባንክ እንደተደወለ አስመስለው የተለያዩ ስልኮችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ ሚስጥር ቁጥር በመቀበል በማጭበርበር ከግለሰቦች አካውንት ብር ከሚመዘብሩ ወንጀለኞች ህብረተሰቡ እንዲጠበቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
በሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለያዩ የባንክ ስሞችን በመጠቀም ለግለሰቦች በመደወል የባንክ አካውንቱን በመናገር ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የባንካችን ተሸላሚ ደንበኛ በመሆንዎ በማለት እና የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን በመጠቀም የሞባይል ባንኪንግ ኮድ እንዲያስገቡ በማግባባት በአካውንት የተቀመጠ ገንዘብን ወደራሳቸው የሚወስዱ አጭበርባሪዎች መበራከታቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ደርሶበታል።
ሕብረተሰቡም ከእንዲህ አይነት የመጭበርበር ወንጀል እራሱን በመጠበቅ ከዚህ በታች በስምና በፎቶ ግራፍ የተገለጹትን ተጠርጣሪዎች ሲመለከት ተቋሙ ያበለፀገውን የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታና ደኅንነት አካላት በአካል በማድረስ የድርሻውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
የታተመበት ቀን:-2024-11-29