ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ
ሰሞኑን የጤና ባለሙያዎች ያነሱትን የመብት ጥያቄ ሽፋን በማድረግ በሀገራችን ትርምስ እንዲፈጠር ከሚሠሩ ኃይሎች ጋር በማበር ሕገ ወጥ የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ፣ በጤና ዘርፉ ላይ ሁከት በመፍጠር እና የታካሚዎችን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል የተጠረጠሩ 47 የጤና ባለሙያዎችን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት ጀምሯል፡፡
እነዚህ ተጠርጣሪዎች የጤና ባለሙያዎች ያነሱትን የደመወዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ እንደሽፋን በመጠቀም ሕገ-ወጥ የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ፤ ሌሎችም ሥራ እንዲያቆሙ ለአድማ በማነሳሰት፣ የታካሚዎች ሕይወት ለሞትና ለአደጋ እንዲጋለጥ በማድረግ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር የተጠረጠሩ ናቸዉ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ የጤና ተቋማት የአድማ መረቦችን በመዘርጋት፤ የጤና ባለሙያ ያልሆኑ አካለትን ነጭ ጋዋን በማስለበስ የሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ገብተዉ ሁከት እንዲፈጥሩ በማድረግ፣ ያልተገባ ወሬ በመንዛት እና በተለያየ መንገድ ሰላማዊ የሕክምና ሂደትን በማደናቀፍ የሕሙማንና የጤና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ሕይወት አደጋ ላይ እንዲወድቅ በማድረግ፣ በመንግሥት የሕክምና አገልግሎት እና ትምህርት በሚሰጥባቸው ተቋማት ውስጥ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲስተጓጎል አድርገዋል፡፡እንዲሁም ሙያቸውን አክብረው በሥራ ላይ በተገኙ ባልደረቦቻቸው ላይ ዛቻ እና ማስፈራራት ከማድረስ ባለፈ ሁከት እንዲፈጠር ሙከራዎችን አድርገዋል ያላቸውን 47 ተጠርጣሪዎች በመረጃና በማስረጃ በመለየት በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጤና ባለሙያዎቹ የሙያው ሥነ-ምግባርና ሕግ በማይፈቅደው ሁኔታ የዜጎችን ሕይወት ለሞትና ለአደጋ በማጋለጥ ሥራ ማቆም፣ ሌሎችም ሥራ እንዲያቆሙ ማነሳሳት እና ማስፈራራት፣ የወንጀል ተግባር መሆኑን እየገለፀ ሌሎችም ከዚህ ተግባር እንዲቆጠቡ ያሳስባል።
በዚህ አጋጠሚ ሕዝባቸውን እና ሕግ አክብረው አገልግሎት እየሰጡ ላሉ የጤና ባለሙያዎች ፖሊስ አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያደርግ እያረጋገጠ፤ ከዚህ ውጭ ሁከትና ብጥብጥን ለማስፋፋት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ፖሊስ እየወሰደ ያለውን ሕጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያሳውቃል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣
ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃንን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ በብሄር እና በሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ የሚያሰራጩ እንዲሁም በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 (አንድ መቶ አስራ አንድ) ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል። ከዚህ ውስጥ በጣም ወጣ ያሉ ብሄርን ከብሄር ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱትን ለይቶ 10 (አስር) ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው ይገኛል።
እነዚህ ግለሰቦች የተለያዩ ግጭት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን በመቅረጽ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት እንዳይረጋጋ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት በብሄር እና በሀይማኖት መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ሲያደርጉ የቆዩ መሆናቸው ይታወቃል።
ተቋሙ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው ክትትል ግለሰቦቹ ምንም አይነት ህጋዊ ፍቃድ የሌላቸውና በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ያልተመዘገቡ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ባሰባሰበው መረጃ ማረጋገጥ ችሏል። ግለሰቦቹ የሚዲያ ተከታዮቻቸውን በመጠቀም ሐሰተኛና ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችን የሚያሰራጩት በክፍያ እንደሆነም በምርመራ ደርሶበታል።
በየትኛውም ሚዲያ ተጠቅመው መረጃን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉ ግለሰቦች የሀገሪቱን ህግና ሥርዓት አክብረው መንቀሳቀስ እና ህጋዊ መስመር በመከተል በተጠያቂነት መንፈስ መስራት ይኖርባቸዋል። ፖሊስም ህግን አክብረው በማይሰሩት ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማሳሰብ ይወዳል፡፡
በመጨረሻም ህብረተሰቡ ያገኛውን መረጃ ሁሉ ከመጠቀም በመቆጠብ በጥንቃቄ መርምሮ ማየትና ማገናዘብ እንዳለበት እያሳሰበ በህግ-ወጥ መንገድ በበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት አጀንዳ ቀርፀው በሀይማኖት፣ በብሄር ህብረተሰቡን ለማጋጨት የሚሰሩ አከላትን በማጋለጥና ለህግ አሳልፎ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ለህዝብ ሲገለጽ እንደነበረው ከሌሎች የጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በመቀናጀት የጀመረውን የህግ ማስከበር ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።
ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ