የኮሚሽነር ጄኔራል መልዕክት

የተከበራችሁ ውድ የሀገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ፖሊስ አመራር እና አባላት እንዲሁም አጋር የፀጥታ አካላት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የለውጥ ሂደት ላይ ትገኛለች።
ዝርዝር መልዕክትአዳዲስ ዜናዎች!
-
"በዕውቀትና በክህሎት የዳበረ ፖሊስ ለተቋም ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየተሰጠ ነው( Federal News)
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢፌፖሚ) "በዕውቀትና በክህሎት የዳበረ ፖሊስ ለተቋም ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አስተዳደራዊ ችግሮችን በመፍታት ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።
-
የትራፊክ አደጋ መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓት የሚያዘምን ሶፍትዌር ወደ ሙሉ ትግበራ መግባቱ ተገለጸ( Federal News)
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ) የትራፊክ አደጋ መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓት የሚያዘምን ሶፍትዌር ከስድስት ወራት የሙከራ ጊዜ በኋላ በዛሬ ዕለት ወደ ሙሉ ትግበራ መግባቱን ተገለጿል።
-
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከክብርት ሸዊት ሻንካ ጋር በትብብር በሚሰሩ ሰራዎች ዙሪያ ተወያዩ( Federal News)
አዲስ አበባ፣ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢፌፖሚ) ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከክብርት ሸዊት ሻንካ ጋር በሁለቱ ተቋማት በትብብር በሚሰሩ ሰራዎች ዙሪያ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ተወያይተዋል።
-
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ መርሃ ግብር በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከበረ( Federal News)
አዲስ አበባ፣ የካቲት 23 ቀን 2017ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ) 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሃ ግብር በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከብሯል፡፡
-
እንኳን ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ( Federal News)
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለመላው የፖሊስ ሠራዊት እያስተላለፈ ፖሊስ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ለሕዝቦቿ ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ እንዲሁም ለህገ-መንግሥት መጽናት፤ የታላቁ የዓድዋ ድል የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና ተላብሶ የሕይወት መስዋዕትነት በመክፈል ሀገራችን ወደ ከፍታ ማማ እንድትገሰግስ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ይገኛል፡፡
-
19ኛው ሀገር ዓቀፍ የፖሊስ ስፖርት ፌስቲቫል በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተጀመረ( Federal News)
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22 ቀን 2017ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ) "በላቀ የስፖርት ተሳትፎ ብቁ እና ንቁ የፖሊስ ሠራዊት እንገነባለን" በሚል መሪ ቃል 19ኛዉ ሀገር አቀፍ የፖሊስ ስፖርት ፌስቲቫል በአበበ ቢቂላ ስታድዮም እየተካሄደ ይገኛል።
የሚሰጡ አገልግሎቶች
የሚሰጡ አስተዳደራዊ አገልግሎቶች
- ጥቆማና አቤቱታ መቀበልና የአቅራቢዎችን ቃል መቀበል
- የህዝብ ክንፍ መድረክ በማዘጋጀት የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት ማረጋገጥና የተቋሙን አፈጻጸም እንዲገመግሙ ማድረግ
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጡ አገልግሎቶች
- የማህበረሰብ አገልግሎት (Community Service) ስራዎችን ማከናወን፣
- ስለወንጀል መከላከልና ምርመራ ሀገር አቀፍ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና አንድ ወጥ የሆኑ የአሠራር ደረጃዎችን ማዘጋጀት
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጤና አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶች
- የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት ለሰራዊቱና ለህግ ታራሚዎች መስጠት፤
- የተኝቶ ህክምና አገልግሎት መስጠት
በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሚሰጡ አገልግሎቶች
በክስ መቀበል አገልግሎት
- የወንጀል ጥቆማዎችንና አቤቱታዎችን መቀበል፣
- የቀረበው አቤቱታ ጥቆማ ወንጀል መሆን አለመሆኑን እና በፌደራል የማጣራት ስልጣን ስር የሚወድቅ መሆን አለመሆኑን መወሰን፣