የኮሚሽነር ጄኔራል መልዕክት

Commissioner Image

የተከበራችሁ ውድ የሀገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ፖሊስ አመራር እና አባላት እንዲሁም አጋር የፀጥታ አካላት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የለውጥ ሂደት ላይ ትገኛለች።

ዝርዝር መልዕክት

አዳዲስ ዜናዎች!

  • በሕገ-ወጥ መንገድ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ሲያንቀሳቅስ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ( Federal News)

    አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም (ኢፌፖሚ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኅብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ብርቱ ክትትል በህገ-ወጥ መንገድ መንገድ ከ5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር (ከአምስት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር) በላይ ሲያንቀሳቅስ የነበረ ግለሰብ ከ25 ግብረ-አበሮቹ ጋር የገንዘብ ልውውጥ ያደርግ መሆኑ አረጋግጦ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራበት መሆኑን ገለፀ፡፡

    በወንጀሉ የተጠረጠረው ሳሙኤል እጓለ አለሙ በቅፅል ስሙ ሳሚ ዶላር የሚባል ሲሆን ነዋሪነቱን በአዲስ አበባ ከተማ በማድረግ ወደ አሜሪካን ሀገር በተደጋጋሚ የሚመላለስ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች፣ የቤት እና የቢሮ እቃዎች እንዲሁም ተዛማጅ መገልገያዎች የችርቻሮ ንግድ ፍቃድን ሽፋን በማድረግ ሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬና በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ተጠርጥሮ በራሱና ዮዲት እጓለ አለሙ ከተባለች እህቱ ጋር በመሆን በስማቸው በተለያዩ ባንኮች በከፈቷቸው ሃያ አምስት የባንክ አካውንቶች በአንድ ዓመት ውስጥ ከ247 ሚሊየን ብር (ሁለት መቶ አርባ ሰባት ሚሊየን ብር) በላይ ማንቀሳቀሳቸውን ፖሊስ ደርሶባቸው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

  • ኢትዮጵያ በ90ኛው ዓለም አቀፍ የፖሊስ ድርጅት (INTERPOL) ጠቅላላ ጉባኤ ተሳተፈች( Federal News)

    ህንድ፣ ኒውደልሂ፣ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም (ኢፌፖሚ) - በህንድ ኒውደልሂ ከተማ እ.ኤ.አ ከጥቅምት 18 እስከ 21 ቀን 2022 በተካሄደው 90ኛው ዓለም አቀፍ የፖሊስ ድርጅት (INTERPOL) ጠቅላላ ጉባኤ ኢትዮጵያ ተሳትፋለች።

    በጉባዔው የ188 አባል ሀገራት ፖሊስ አዛዦች፣ ፖሊስ ተጠሪ የሆኑላቸው ሚኒስትሮች እና የተለያዩ ከፖሊስ ጋር በአጋርነት የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራ ልዑካን ቡድንም ተሳትፏል።

  • የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት( Commissioner Message)

    የተከበራችሁ ውድ የሀገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ፖሊስ አመራር እና አባላት እንዲሁም አጋር የፀጥታ አካላት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የለውጥ ሂደት ላይ ትገኛለች።

  • የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት( Commissioner Message)

    የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

    በቅድሚያ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለሀገራችን የፖሊስ አባላት እንኳን ለ2015 ዓ.ም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያልኩ፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መላውን ሕዝብ ከጎኑ አሰልፎ በአዲስ ዓመት ካለፈው የተሻለ አንፀባራቂ ውጤት በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ብሩህ ተስፋና የተቋማችንን ከፍታ የሚያረጋግጥበት ዘመን እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ።

  • ከ44 ሺህ በላይ የሽጉጥ ጥይት ተያዘ( Federal News)

    ጎንደር ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም (ኢፌፖሚ):- መነሻውን ሁመራ በማድረግ ወደ ማዕከላዊ ጎንደር በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ44 ሺህ በላይ የተለያዩ የሽጉጥ ጥይቶች መያዛቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

    ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝውውር ወደ ተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በማሰራጨት ሁከት ለመፍጠር የሚጥሩ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ሙከራቸው በየጊዜው በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ ጠንካራ ክትትል እየከሸፈባቸው ይገኛል፡፡

  • የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ በኮልፌ ልዩ ልዩ ፖሊስ ማሰልጠኛ ግቢ ችግኝ ተከላ አካሄደ( Federal News)

    አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 04 ቀን 2014 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፡- የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ከኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ስራ አስፈፃሚዎች ጋር በመቀናጀት በኮልፌ ልዩ ልዩ ፖሊስ ማሰልጠኛ ግቢ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሀገራዊ መርሀ ግብሩን ተከትለው የችግኝ ተከላ አካሂዷል።

    “ችግኝ ተክዬ ሳንባዬን አድሳለሁ፤ በችግኙ የዝናብ ጠብታ ግድቤን እሞላለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት የችግኝ ተከላ ባካሄዱበት ወቅት በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ችግኝ በመትከል ንግግር ያደረጉት ክቡር ምክትል ኮምሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ ችግኝ ተክለን ሀገራችንን አረንጓዴ የማልበስ ጉዳይ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነና አመርቂ ውጤትም እየተመዘገበ እንደሆነ ተናግረው አመቺውን የክረምት ወቅት በመጠበቅ ችግኝ መትከል ለሀገራችን ልማትና ዕድገት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

የሚሰጡ አገልግሎቶች

ወንጀል መከላከል


የፌዴራል መንግሥት ተቋማትን ይጠብቃል፤ ለከፍተኛ የፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ለውጭ አገር የክብር እንግዶችና ዲፕሎማቶች ጥበቃ ያደርጋል፤


አስተዳደርና ልማት


በፖሊስ ምልመላና ቅጥር፣ በትምህርትና ሥልጠና፣ በማዕረግ አሰጣጥ፣ በደንብ ልብስ አለባበስ፣ በትጥቅና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ሀገር አቀፍ ደረጃዎችን ያወጣል፤


ወንጀል ምርመራ


የወንጀል ምርመራን በተመለከተ ከፍትሕ ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር በጋራ ይሠራል፤


ወንጀል መከላከል


በሕገ-መንግሥቱና ሌሎች ህጎችን፣ በመንግሥትና በሀገር ፀጥታ እና በሰብዓዊ መብት ላይ የሚፈፀሙ ማናቸውም ዓይነት የወንጀል ስጋቶችና ድርጊቶችን ይከላከላል፡፡